ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገለጹ

1 Day Ago 117
ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገለጹ
በሲዳማ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለፁ።
 
ርዕሰ መስተዳድሩ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኀን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
 
በባለፉት የለውጥ ዓመታት የክልሉን ህዝብ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተጀመሩ ስራዎች ሁሉን አቀፍ ለውጥ እየታየ ይገኛል ብለዋል።
 
በዚህም በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ በእንሰሳት ሐብት ልማት እና በሌሎችም ዘርፎች የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል።
 
በገጠር እና ከተማ ባሉ የሐብት አማራጮች የስራ እድል ለመፍጠር በተከናወኑ ስራዎች በባለፉት አራት ዓመታት ለ300 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ጠቅሰዋል።
 
ከዚህ ባለፈም የቤተሰብ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በ8 ኢንሼቲቭ በ68 ፓኬጆች ተቀርፀው እየተተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
 
መንግሥት በቀጣይም በልማት፣ መልካም አስተዳደር እና በዴሞክራሲ ሥረዓት ግንባታ ለህዝብ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ርዕሰ መስተዳድሩ በማብራሪያቸው ገልጸዋል።
 
በሚካኤል ገዙ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top