ወላጅ እናቴ መታጠቢያ ቤት ወድቃ ያጋጠማት የእግር ስብራት ዛሬ ለማደርገው የሰብዓዊ ድጋፍ መሰረቱ ነው ይላል ዶ/ር ልሣነወርቅ ሆንሲቦ።
በወቅቱ የነበረውን ሁኔታም ሲያስረዳ፣ እናቴ ሕክምና እንድታገኝ ወደ ጤና ተቋም አምርተን ሐኪሞች እስከሚመጡ እርሷ እና ሌሎች ታካሚዎች ይጠብቁ ነበር፤ እኔም ያንን ስመለከት ለሰዎች መድረስ የሚችል የሕክምና ባለሙያ መሆን አለብኝ ስል አሰብኩ በማለት ያስታውሳል።
በዚህ መነሻነት የተጀመረው የሕክምና ትምህርት ዛሬ ላይ ለብዙ ወገኖች በመድረስ ለሕመማቸው መፍትሄን ሰጥቷል።
የመኖሬ እና የመማሬ ምክንያት በማይመቹ አካባቢዎች ያሉ ወገኖቼን ማገዝ ነው ይላል የራዲዮ ተቋም መስራች እና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ልሣነወርቅ ሆንሲቦ።
በበርሃማ እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በተደረጉ 12 የሕክምና ዘመቻዎች ከ50 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ችሏል።
በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ስንቀሳቀስ የሁሉንም ማህበረሰብ ሁኔታ ተጋርቼ ነው፤ በዚህም አቅጄው የተማርኩለትን ዓላማዬን ማሳካት እንደቻልኩ ይሰማኛል ሲል ይገልፃል።
የዶ/ር ልሣነወርቅ ሰብዓዊ ድርጊት ዓለም አቀፍ ተቋም በሆነው ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ እውቅናን እንዲያገኝም አስችሎታል።
ዶ/ር ልሣነወርቅ፤ ባልደረስኩባቸው የሀገሪቷ ክፍሎች ያላገኘኋቸው ማህበረሰቦችን ማግኘት እና ማገዝ ቀጣይ እቅዴ ነው ሲልም ተናግሯል።