የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያከናወናቸው ባሉ የምክክር ሂደቶች አጀንዳን አግባብነት ባላቸው በተለያዩ መንገዶች እየሰበሰበ ይገኛል፡፡
ኮሚሽኑ በሂደቱ ውስጥ እጅግ በርካታ ሊባሉ የሚችሉ አጀንዳዎችን እየተረከበ እንደሚገኝ ነው፡፡ እነዚህን አጀንዳዎች ሲረከብ የትኞቹን መርሆዎች በመተግበር የአጀንዳዎችን አግባብነት ይመረምራል የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱ ተገቢ ነው፡፡
የአጀንዳ ሀሳቦች ጥልቀት እና አግባብነት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ላይ ከሀገራዊ ምክክር መርሆዎች እንዱ እንደሆነ ተደንግገጓል፡፡ በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች የአጀንዳ ሀሳቦች ጥልቀት እና አግባብነት ዘላቂ መፍትሔን ሊያስገኝ የሚችል እና ውጤታማ የምክክር ሂደቶች ለማድረግ ዓይነተኛውን ሚና ይጫወታል፡፡
ነገር ግን የአጀንዳ ሀሳቦች ጥልቀት እና አግባብነት በየትኞቹ መስፈርቶች ይመዘናል?

ታሪካዊ ዓውድን መሰረት በማድረጋቸው

የተለያዩ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና የፖለቲካ ዘርፎችን ያማከሉ ብሎም ሁለንተናዊ አካታች በመሆናቸው

በመረጃ እና በማስረጃ የተደገፉ በመሆናቸው

ዘለቄታዊና እና በጎ ተፅዕኖን ሊያስከትሉ የሚችሉ በመሆናቸው በሚሉት መስፈርቶች ይለያሉ፡፡

የሕዝብን እና የሀገርን ጥቅም በማስቀደማቸው

ሀገራዊ ምክክሩ ከቆመለት ዓላማ ጋር መስማማታቸው

ወካይ፣ አስቸኳይ እና አስፈላጊ መሆናቸው

ነባራዊ ሀኔታን እና ዕውነታውን ያገናዘቡ መሆናቸው

ግጭትን መቅረፍ መቻላቸው በሚሉት መስፈርቶች ይለያሉ፡፡