የኢትዮጵያን የማንሠራራት ጉዞ የሚሳካው በተቋሞቻችን ጥንካሬ ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

2 Days Ago 91
የኢትዮጵያን የማንሠራራት ጉዞ የሚሳካው በተቋሞቻችን ጥንካሬ ነው፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
የኢትዮጵያ የማንሠራራት ጉዞ የሚሳካው በተቋሞቻችን ጥንካሬ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
 
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ አስፈጻሚ አካላትን የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ዛሬ መገምገማቸውን ገልጸዋል።
 
የኢትዮጵያን የማንሠራራት ጉዞ የሚሳካው በተቋሞቻችን ጥንካሬ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ባለፉት ሥድስት ዓመታት መንግሥት ለጠንካራ ተቋማት ግንባታ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን ጠቅሰዋል።
 
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ራሳቸውን በአግባቡ በማደራጀት ለሀገር ግንባታ የሚቆጠር አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ እንደሆኑም አንስተዋል።
 
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአብነትም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስኮች ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች የተቋሞቻችን የመፈጸም አቅም ማሳያ ናቸው ሲሉ ጠቅሰዋል።
 
በቀጣይም ተቋማቱ የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ለማሳካት አገልግሎት አሰጣጣችንን ማዘመን፣ ወጪ ቆጣቢ አሰራርን መከተል፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እና በተሰጠን ተልዕኮ የምንፈጥረውን በጎ ተፅዕኖ እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን በቀጣይነት እየገመገሙ መሄድ አስፈላጊ መሆኑን አቅጣጫ አስቀምጠናል ብለዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top