ሴቶችን ማስተማር ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል - ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው

10 Mons Ago 868
ሴቶችን ማስተማር ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል - ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው "እሷን አስተምሩ እና አፍሪካን ለውጡ" በሚል መሪ ቃል በ28ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ድርጅት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በንግግራቸውም፤ ሴቶችን ማስተማር ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በተጨማሪ መብታቸውን አውቀውና አስከብረው በነጻነት እንዲኖሩ የማድረግ ጉልህ  ሚና አለው ብለዋል፡፡

በቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት ሴቶችን ለማስተማርና ለማብቃት የተሰሩ ስራዎችን በጉባኤው ላይ ማብራራታቸውንም ከቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top