በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይተገበራል - የትምህርት ሚኒስቴር

10 Mons Ago
በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይተገበራል - የትምህርት ሚኒስቴር

በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሚኒስቴሩ በትምህርት ዘርፉ ላይ የተደረገውን ለውጥና የተከናወኑ ስራዎችን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በአጠቃላይ ስርዓተ ትምህርቱ ላይ የነበረውን ስብራት ለመጠገን መሰረት የሚጥሉ የለውጥ ስራዎች መከናወናቸውንም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ገልጸዋል።

በዚህም በ2015 ዓ.ም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ተግባራዊ መደረጉን አመልክተዋል።

በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱን ስርዓተ ትምህርት በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያግዙ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች እንዲኖሩም በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በኦንላይን እንደሚሰጥም ኢዜአ ዘግቧል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top