የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ዝቅተኛ ካርበን ልቀት ልማት ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

341 Days Ago
የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ዝቅተኛ ካርበን ልቀት ልማት ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ዝቅተኛ ካርበን ልቀት ልማት ስትራቴጂ (LT-LEDS) ይፋ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል መንግሥታት የስራ ኃላፊዎች፣ ቁልፍ የልማት አጋር ድርጅቶች፣ የገንዘብ ድጋፍ ሰጪ አካላት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቾች በተገኙበት ነው ይፋ የሆነው።

የልማት ስትራቴጂው ለሚቀጥሉት 30 ዓመታት ኢትዮጵያ የምትመራበት ይሆናል ተብሏል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ተደጋጋሚ ድርቅ እየተከሰተና ኢኮ ሲስተም እየተዛባ እንደሀገር እየተፈተንን እንገኛለን ብለዋል።

ይህን ለመቋቋምም ኢትዮጵያ የተለያዩ ፕሮግራሞች ነድፋ እየተገበረች መቆየቷን ገልፀዋል።

ለአብነትም የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም እንዲሁም የኃይል ልማት ዘርፍ እና የታዳሽ ኃይል ልማት ፕሮግራምን ጠቅሰዋል።

ስትራቴጂው ኢትዮጵያ እየተገበረችው ላለው የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ቁልፍ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

ስትራቴጂው እ.ኤ.አ በ2015 ከፀደቀው የፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ጋር የተጣጣመ መሆኑም ተገልጿል።

በሞላ አለማየሁ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top