የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 - ሚያዚያ 15 እንደሚከናወን ተገለፀ

1 Yr Ago
የዘንድሮውን  የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 - ሚያዚያ 15  እንደሚከናወን ተገለፀ
የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 - ሚያዚያ 15፣2015ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገለፀ።
አገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተናን የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር)መረጃዎችን በትክክል ባለመሙላት የሚፈጠሩ ችግሮችን ለማስቀረት ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱና በጥንቃቄ ማስመዝገብ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
ያልተመዘገበ ተማሪ የ 2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን እንደማይፈተንም ዶ/ር እሸቱ ገልፀዋል።
ምዝገባው ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች በመንግስት የመደበኛ ትምህርት ቤቶች ሲሆን ፣ ለድጋሜ ተፈታኞች እና የርቀት ትምህርት ተማሪዎች በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች አማካኝነት በበይነ መረብ ብቻ እንደሚያካሂዱ ኃላፊው አመልክተዋል።
መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ 9-12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም በመማር ላይ ያሉ መሆን ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል።
ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top