ከጎረቤት ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያን በማስገባት ላይ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

8 Mons Ago
ከጎረቤት ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያን በማስገባት ላይ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ከጎረቤት ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያን በማስገባት ላይ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ከእነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
ብሬን እና ክላሽንኮቭ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያን ከመሰል ጥይቶች ጋር ከጎረቤት ሀገር ጭነው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ኦሞ ዞን ሀመር ወረዳ የኦሞ ወንዝን በጀልባ በማሻገር በሞተር ሳይክል እየጫኑ እንዳሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማዕከላዊ ወንጀል ኢንተለጀንስ ከአካባቢው ፖሊስና ኅብረተሰብ ጋር በመተባባር ባደረገው ኦፕሬሽን አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
በተመሳሳይ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአካባቢው ፖሊስና ኅብረተሰብ ጋር ባደረገው ኦፕሬሽን በአማራ ክልል የተለያዩ ሽጉጦች፣ ዘጠኝ ክላሽንኮቭ፣ 13 ቦምቦች እና የተለያዩ በርካታ ጥይቶች በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ስድስት ተጠርጣሪዎችን ከነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top