በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለው የሥራ እንቅስቃሴ አበረታች ነው፦ የአሜሪካ የውጭ ንግድ ጉዳይ ካውንስለሮች

1 Yr Ago
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለው የሥራ እንቅስቃሴ አበረታች ነው፦ የአሜሪካ የውጭ ንግድ ጉዳይ ካውንስለሮች
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለው የሥራ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን የአሜሪካ የውጭ ንግድ ጉዳይ ካውንስለሮች ገለጹ።
 
 
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የውጭ ንግድ ጉዳይ ካውንስለሮች ቡድን በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለውን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
 
 
ካውንስለሮቹ በጉብኝታቸው በኢንዱስትሪ ፓርኩ ያለውን የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከቱ ሲሆን ከአጎዋ ተጠቃሚነት ዕድል መቋረጥ ጋር ተያይዞ ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ በፓርኩ ከሚሠሩ ባለሀብቶች ጋር መወያየታቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
 
 በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ22 በላይ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ኢንቨስት በማድረግ ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ፈጥረው በመሥራት ላይ ይገኛሉ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top