የግብርና ሚኒስቴር ከልማት አጋር አካላት ጋር በመሆን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ394 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

1 ዓመት በፊት 270
የግብርና ሚኒስቴር ከልማት አጋር አካላት ጋር በመሆን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ394 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

የግብርና ሚኒስቴር ከልማት አጋር አካላት ጋር በመሆን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ394 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ 

********************

የግብርና ሚኒስቴር ከልማት አጋር አካላት ጋር በመሆን በኦሮሚያ፣ደቡብ እና ሱማሌ ክልሎች በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ394 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

በግብርና ሚኒስቴር የእንሰሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ድጋፉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ ድጋፉ እንደ የክልሎቹ ፍላጎት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰብል ዘር መግዣ፣ ለመኖ ዘር መግዣ እና ለእንስሳት መድኃኒት መግዣ እንደሚውል ገልፀዋል።

ከቀረበው የገንዘብ ደጋፍ ውስጥ 170 ሚሊየን ለኦሮሚያ ክልል፣ 64 ሚሊየን ብር ለደቡብ ክልል እንዲሁም 160 ሚሊዮን ብር ለሱማሌ ክልል እንደሚከፋፈልም ነው ሚኒስትር ደኤታው የገለፁት።

በወይንሸት ደጀኔ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top