የዓይን ሞራ ግርዶሽ (Cataracts)

1 Yr Ago 2101
የዓይን ሞራ ግርዶሽ (Cataracts)


የዓይን ሞራ ግርዶሽ በማንኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ሊከሰት ቢችልም ብዙውን ጊዜ ግን ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣ እና የዓይን ሌንስ ብርሃን እንዳያስተላለፍ በነጭ ሞራ መሳይ ነገር በመሸፈን ዓይነ ስውርነትን የሚያስከትል ችግር ነው፡፡

የዓይንን ሌንስ በተፈጥሮ ወይም በጤናማ ሰው ላይ ግልፅ ነው።

 አብዛኛዎቹ የዓይን ሞራ ግርዶሾች በጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ እየተባባሱ ይሄዳሉ ፡፡ በሁሉም ሰው ማለት ይቻላል እይታን በሚመልስ መልኩ በሕክምና ሂደት የዓይን ሞራ ግርዶሽ በቀዶ ሕክምና ሊወገድ ይችላል።

የዓይን ሞራ ገርዶሽ እንዴት ሊከሰት ይችላል?

  • የእድሜ መጨመር
  • ለፀሀይ ብርሃን አብዝቶ መጋለጥ
  • በዓይን ላይ በሚደርስ ጉዳት
  • በስኳር ህመም
  • እንዲሁም የተለያዪ የመድሀኒት ዓይነቶች ለዓይን ሞራ ግርዶሽ መንስኤ ሊሆን ይችላል።
  • አንዳንዴም ህፃናት ከዓይን ሞራ ግርዶሽ  ጋር ሊወለዱም ይችላሉ።


የዓይን ሞራ ግርዶሽ(ካታራክት) ምልክቶች ምንድን ናቸው?

  • የዓይን ብዥታ ፣ መደብዘዝ ወይም በዳመና የተጋረደ የሚመስል እይታ የፀሐይ ወይንም የመብራት ብርሃን በሚያዪ ጊዜ በጨረር መብዛት ምክንያት በጨለማ መኪና ለማሽከርከር መቸገር ይገጥሟል።
  • በአንደኛው ዓይናችን ብዥታ የመኖር ሁኔታ የሞራ ግርዶሽ (ካታራክት) ሙሉ ለሙሉ እይታን እንዳይኖረን የሚያደርገው እጅግ ዝግመታዊ በሆነ ሁኔታ ሲሆን አንዳንዴም ምንም ዓይነት የእይታን ችግር ላይፈጥርም ይችላል።

 
የዓይን ሞራ  ግረዶሽ ህክምናው

  • የቀዶ ጥገና የዓይን ሞራ ግርዶሽ  የማከሚያ መንገድ ሲሆን ይህም የሚደረገው በሞራ ግርዶሽ (ካታራክቱ) ምክንያት የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን ለመግፋት የሚከብድ ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው።
     የካታራክት ህመምን በህክምና ባለሞያ የታዘዘ መነፅር በማድረግ የእይታ ችግሩን በመጠኑም መቀነስ የሚቻል መሆኑን የዶክተር አለ የጤና ምክር ያሳያል።
  • ከካታራክት ጋር የሚወለዱ ህፃናትና በዓይን ላይ በሚደርስ ጉዳት ምክንያት የሚከሰቱ የካታራክት ችግሮች የቆዳ ጥገና ህክምና ያስፈልጋቸዋል።


 ካታራክትን እንዴት መከላከል ይቻላል?

የዓይን ሞራ ግርዶሽ ወይም ካታራክትን መከላከል የሚቻልበት መንገድ ባይኖርም ካታራክት እድገቱን ግን በዝግታ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል፤ ይህም፡-

  • ሲጋራ ማጤስ በማቆም
  • የፀሐይ መከላከያ መነፅር ወይንም ኮፍያ በማድረግ
  • ጤናማ አመጋገብ መከተል
  • እንዲሁም የስኳር ህመም ካለ መቆጣጠር ተገቢ ነው። 

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top