አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል።
የግሩፕ ሥራ አመራር ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት፣ ከዋና ሥራ አስፈጻሚ በተጨማሪ ሁለት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችንም መድቧል።
አቶ መሐመድ ጀማል ሸሪፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ እና ወ/ሮ መሠረት ደስታ ገ/ኢየሱስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የምርምር እና ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ዘርፍ ኃላፊ በመሆን ተመድበዋል።
በግሩፑ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በዶ/ር አብረሃም በላይ ተፈርሞ በወጣው ደብዳቤ መሠረት የሥራ ኃላፊዎቹ ከጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተመድበዋል።
ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የነበሩት አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በቅርቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሾማቸው ይታወሳል።