የምሽቱን የአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታየመሩት ባምላክ ተሰማ አድናቆት እየጎረፈላቸው ነው።

2 Yrs Ago
የምሽቱን የአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታየመሩት ባምላክ ተሰማ አድናቆት እየጎረፈላቸው ነው።
የምሽቱን የአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የመሩት ባምላክ ተሰማ አድናቆት እየጎረፈላቸው ነው
**************************
ሴኔጋል ቡርኪናፋሶን 3 ለ1 በረታችበት የምሽቱ የግማሽ ፍፃሜ ፍልሚያ ጨዋታውን የመሩት ባምላክ ተሰማ አድናቆት እየጎረፈላቸው ነው፡፡
በትላንትናው ምሽት አራት ሰዓት ላይ የተደረገውን የሴኔጋል እና የቡርኪናፋሶ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በጥሩ ብቃት መምራታቸውን ለእግር ኳሱ ቅርበት ያላቸውን የዘርፉ ግለሰቦች አስተያየት አካቶ ዴይሊ ሜል ዘግቧል።
ኢትዮጵያዊው ዳኛ ባምላክ ለአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ለማለፍ የሚደረገውን ወሳኝ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በዋና ዳኝነት በብቃት መምራቱን ከተለያዩ ሀገራት የተላኩ የቲውተር መልእክቶችን በመሰብሰብ ዴይሊ ሜል በልዩ ሁኔታም አስነብቧል።
የሴኔጋልና ቡርኪናፋሶ ብሄራዊ ቡድኖች ባደረጉት ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ የነበሩት የዳኛው ውሳኔ ከብዙ ተመልካቾች ዘንድ ሙገሳዎች እንዲጎርፉለት አድርጓል።
አንደኛው ውሳኔ የቡርኪናፋሶ ግብ ጠባቂ ሄርቭ ኮፊ ከሴኔጋሉ አማካይ ቺኮ ኮያቴ ጋር የተፈጠረው ግጭት በቪዲዮ የታገዘ የዳኝነት ስርዓት/VAR/ ታግዘው የሰጡት ውሳኔ አስገራሚ የዳኝነት ክህሎት እንዳላቸው የሚያሳይ ነው ብሏል ዘገባው።
ሌላኛው አጋጣሚ ደግሞ ኤድሞንድ ታፕሶባ "በእጅ ኳስ ነክቷል" በሚል አስቀድሞ ቢጫ ተሰጥቶ በተመሳሳይ በቪዲዮ የታገዘ የዳኝነት ስርዓት የሻሩበት የዳኛው ውሳኔ፣ የዳኛውን እርጋታ እና በፈገግታ የታጀበ ውሳኔ በብዙዎች ዘንድ አድናቆት ተችሮታል።
እንዲያውም እንደዴይሊ ሜል ዘገባው ከባምላክ የዳኝነት ብቃት የእንግሊዝ ዳኞች ሊማሩ ይገባል ሲል ደምድሟል፡፡
በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ከታዩ ዳኝነቶች "ምርጡ ዳኛ" በሚል ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ በእግር ኳስ ደጋፊዎች መሞካሸታቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡
የስፖርት ጋዜጠኞች እና የእግር ኳስ ወዳጆቼ ባምላክ ተሰማን "የአፍሪካ ምርጡ ዳኛ፣ የአለም ምርጡ ዳኛ፣ የጨዋታው ኮከብ፣ ሀገሩንም አፍሪካንም ያኮራ፣ የቫር አጠቃቀም የገባው ብልህ፣ ከተጫዋቾች ጋር በጓደኝነት ስሜት የሚላመድ፣ ወዘተ እያሉ አድናቆት እያጎረፉለት ነው።
ምሽቱን በተካሄደው ጨዋታ ሴኔጋል ቡርኪናፋሶን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ስታሸንፍ፣ የሴኔጋልን የማሸነፊያ ግቦች አብዱል ዲያሎ፣ ዴይንግና ሳዲዮ ማኔ አስቆጥረዋል፡፡
በዛሬው የአፍሪካ ዋንጫው የግምሽ ፍፃሜ ሲቀጥል ምሽት 4፡00 ካሜሩን ከግብጽ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top