ክሪስታል ፓላስ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በዩሮፓ ሊግ መሳተፍ እንደማይችል የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታውቋል።
ፓላስ ከብዝሀ ክለብ ባለቤትነት ሕግ ጋር በተያያዘ ከዩሮፓ ሊግ ወደ ኮንፈረንስ ሊግ ለመውረድ ተገዷል።
በፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን ባለቤት ጆን ቴክስተር የሚተዳደረው ፓለስ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤፍኤ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ በዩሮፓ ሊግ የመሳተፍ ዕድል ቢያገኝም፤ በብዝሀ ክለብ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እድሉን አጥቷል።
በሊጉ 12ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ፓለስ በፈረንሳይ ሊግ ዋን ከሚሳተፈው ሊዮን ያነሰ ደረጃ ላይ መገኘቱ ከውድድሩ እንዲወጣ አድርጎታል።
ውሳኔውን ተከትሎ ሊዮን በዩሮፓ ሊግ ሲሳተፍ የእንግሊዙ ተወካይ ወደ 3ኛው የአውሮፓ ውድድር ኮንፍረንስ ሊግ ዝቅ እንዲል ሆኗል።
በሴራን ታደሰ