በሶማሊያ ከ30 አመታ በኋላ በተካሄደው ታሪካዊው የእግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ሚና ምንድን ነው?

منذ 2 أيام
በሶማሊያ ከ30 አመታ በኋላ በተካሄደው ታሪካዊው የእግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ሚና ምንድን ነው?

የጎረቤቶቿን ችግር እንደራሷ የምትመለከተው ኢትዮጵያ ለጎረቤት  ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጥ የዲፕሎማሲ ፖሊሲን በመከተል  በሶማሊያ የሰራችው ስራ ፍሬው እየታየ ነው።

ሰላምና መረጋጋት የማስፈን እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የማስጀመር ጥረቷ በስፖርቱ ዘርፍ መነቃቃትን እስከመፍጠር ደርሷል።

የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር እግርኳስ ግጭቶችን በማስወገድ ወንድማማችነትን ለመፍጠር ወሳኝ ድርሻ አለው በሚል ከአቻ ማህበራት ጋር በመተባበር የቀድሞ እግርኳስ ተጫዋቾች ወደ ሶማሊያ የሰላም ጉዞ  እንዲያደርጉ አድርጓል።

የአፍሪካ የእግር ኳስ ከዋክብት ወደ ሞቃዲሾ በማቅናት ሰላምን ወንድማማችነትን ሰብከዋል።

የእግርኳስ ፈርጦቹ ወደ ሶማሊያ ለማቅናት የመረጡት የአህጉሪቱን ኩራት የኢትዮጵያ አየርመንገድ ነው።

ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ከሌሎች ጎረቤቶቿ ጋር መስዋዕትነት የከፈለችው ኢትዮጵያ ሞቃዲሾ የናፈቀችው ስፖርታዊ ውድድር እንዲጀመር በአየርመንገዷ በኩል የድርሻዋን አበርክታለች።

በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ድጋፍ "እግር ኳስን ለዘላቂ ሰላምና እርቅ" የመጠቀም ባህል ለማሳደግ የቀድሞው ኮከቦች ሞቃዲሾ በመገኘት  ከሶማሊያ የቀድሞው ተጫዋቾች ጋር የሰላም ጨዋታ አድርገዋል።

ታሪካዊው ጨዋታ የአልሻባብ ማሰልጠኛ ማዕከል በነበረው የሶማሊያ ስታዲየም ነው የተካሄደው።

ጨዋታው ሀገሪቱ  በአልሸባብና ጥቃትና ባጋጠማት የፖለቲካ ቀውስ አማካኝነት የደፈረሰውን ገፅታዋን በመገንባት ወደ ዓለም መድረክ እንድትመለስ ለማድረግ ያግዛል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

እነ ሳሙኤል ኤቶ፣  ጄጄ ኦካቻ እና ኢማኑኤል አዲባየርን ያካተተው የአፍሪካ የቀድሞ ከዋክብት ቡድን የሶማሊያ አቻውን 8 ለ 4 አሸንፏል።

ጨዋታው ለሶማሊያም እንደ ሀገር ድል ያደረገችበት ነው፤ ሶማሊያውያን ወጣቶች ስታዲየም በመገኘት ለእግር ኳስ፣ ለሰላም፣ ለልማት ያላቸውን መሻት ለዓለም አሳይተዋል፡፡

የሰላም እግርኳስ ግጥሚያው ከ30 ዓመታት በኋላ  በሀገሪቱ የተካሄደ ታሪካዊ ክስተት  እንደሆነ የተናገሩት የሀገሪቱ የሶማሊያ  ወጣቶች ስፖርት ሚኒስትር  መሐመድ አቡዱልቃድር አሊ፥ ሶማሊያ  አሁን ካለችበት ሁኔታ ወደ ሰላም ለምታደርገው ጉዞ  አጋዥ ነው ብለዋል።

በሶማሊያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር እንዲሁም የእግር ኳስ ስፖርት መልሶ እንዲያንሰራራ ለማድረግም ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ነው ያነሱት።

ጨዋታው የሶማሊያን ገፅታ ለመገንበታ ትልቅ አስተዋፅ እንዳለው የተናገሩት የሀገሪቱ የፀጥታ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ  አሊ ሀጋ፥ ሶማሊያ የአፍሪካ ዋንጫን ማስተናገድ እንደምትችል ያሳያል ብለዋል፡፡

ሞቃዲሾ የሰላም ጨዋታውን ካፍና ፊፋ ውድድሮችን እንዳታስተናግድ የጣሉባትን እገዳ እንዲያነሱላት ጫና ለመፍጠርና ወደ  አህጉራዊና አለማቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮች ለመመለስ ቁርጠኛ መሆኗን አሳይታበታለች ተብሏል።

ሶማሊያ ሰላሟ በአንጻራዊነት ተመልሶ ስፖርታዊ ውድድሮችን ማስተናገዷን እንድትቀጥል በልጆቿ መስዋዕትነት ከፍተኛ ዋጋ የከፈለችውና በሰላም ተጓዦቹ አየርመንገዷ ተመራጭ ከሆነችው ኢትዮጵያ ጋር አብሮ መስራት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ብዙዎች ይመክራሉ።

በላሉ ኢታላ


ردود الفعل
Top