ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ በቀጠለው የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት የሟቾች ቁጥር 16 ደረሰ

1 Day Ago 218
ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ በቀጠለው የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት የሟቾች ቁጥር 16 ደረሰ

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማ የተከሰተው የሰደድ እሳት አሁንም ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

በተከሰተው ሰደድ እሳት ምክንያት እስካሁን 16 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተጠቅሷል፡፡  

እንዲሁም በአደጋው ከ137 ሺህ በላይ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው መፈናቀላቸው ተነግሯል፡፡

ሰደድ እሳቱ 135 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመት ማድረሱ የተገለፀ ሲሆን፣ ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ነው የተገለጸው።

በካሊፎርኒያ ባለው ሳንታ ሞኒካ ተራራ መነሻውን ያደረገው ይህ ሰደድ እሳት በአካባቢው ያለው ከፍተኛ ንፋሳማ የአየር ሁኔታ ሰደድ እሳቱ በቶሎ እንዲስፋፋ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ እሳቱን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ቢቀጥልም፤ በሎስ አንጀለስ የተለያዩ ስፍራዎች ለሚገኙ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ወይም ለመውጣት እንዲዘጋጁ ተነግሯቸዋል ተብሏል።

በርካታ የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተሮች እና አውሮፕኖች እሳቱን ለማጥፋት አሁንም ርብርብ ማድረጋቸውን እንደቀጠሉም ተጠቅሷል።


Feedback
Top