የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ የይርጋለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ የኦክሲጂን ማምረቻ ፋብሪካ መርቀዋል።
ፋብሪካው በቀን ከ190 በላይ በባለ 50 ሊትር ሲሊንደር ኦክስጂን ማምረት የሚችል ሲሆን፤ ለይርጋለም ሆስፒታል እና አቅራቢያ ለሚገኙ የመንግሥት ጤና ተቋሟት አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።
የፋብሪካው ስራ መጀመር የሆስፒታሉ እና በአቅራቢያ የሚገኙ የጤና ተቋሟት የኦክሲጅን ፍላጎትን በሟሟላት የተሻለ አገልግሎት ለመሰጠት እንደሚያችልም ተጠቁሟል።
ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በዚሁ ወቅት፤ አስቀድሞ መከላከል ካልሆነ ደግሞ አክሞ ለማዳን እንዲቻል የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ 45 የኦክሲጅን ፋብሪካዎች በመንግሥት እና በግል ተቋሟት ተቋቁመው አገልግሎት እየሠጡ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተለይ ኦክሲሲጅን አክሞ ለማዳን ካለው አስፈላጊነት አንፃር ለአገልግሎቱ ተደራሽነት መንግስት በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልፀዋል።
ለፋብሪካው ግንባታ በጤና ሚኒስቴር ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተገልጿል።
በሚካኤል ገዙ