አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ህግ ልታወጣ ነው

1 Mon Ago 263
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ህግ ልታወጣ ነው

አውስትራሊያ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ህግ ልታዘጋጅ መሆኗን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ ተናገሩ።

የማህበራዊ ሚዲያ ልጆች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን የተናገሩት  ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዓለም ሀገራት ምሳሌ መሆን የሚችል ህግ ይዘጋጃል ብለዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ ረቂቅ ህጉ እ.ኤ.አ. በ2024 እንደሚዘጋጅና በሚቀጥለው ዓመት ለህግ አውጪ ምክር ቤት እንደሚቀርብ አስታውቀዋል።

በሀገሪቱ ጥቅም ላይ በዋሉ በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ አውታሮችን ተከታትሎ  ግብረ-መልስ የሚሰጥና ትክክለኛ እርምጃዎችን የሚወስድ አካል እንደሚኖርም ነው ያስታወቁት።

በአውስትራሊያ ልጆች የማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ ለማድረግ የቀረበውን ህግ የማውጣት ሀሳብ በሀገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚገኙ ሁለቱ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ድጋፍ ማግኘቱን አልጃዚራ ዘግቧል።

አውስትራሊያ እ.ኤ.አ. በ2024 የሀሰተኛ መረጃ ስርጭን ለመቆጣጠር እና የኦንላይን የተጠቃሚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ግዴታቸውን የማይወጡ የቴክኖሎጂ ተቋማትን መቅጣት የሚያስችላትን ህግ ማውጣቷ ይታወሳል።

በላሉ ኢታላ


Feedback
Top