33ኛው የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያና የፀጥታ ኃላፊዎች መደበኛ ስብሰባ በኪጋሊ እየተካሄደ ነው

منذ 31 أيام
33ኛው የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያና የፀጥታ ኃላፊዎች መደበኛ ስብሰባ በኪጋሊ እየተካሄደ ነው

የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ክልላዊ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈን "የሁለት አስርት ዓመታት ቁርጠኝነት” በሚል መሪ ሃሳብ 33ኛው የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያና የፀጥታ ኃላፊዎች መደበኛ ስብሰባ በሩዋንዳ ኪጋሊ እየተካሄደ ይገኛል።

ውይይቱ በቀጣናው ውስጥ መረጋጋትን እና ደህንነትን ለማስጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተጠቅሷል።

በመከላከያ የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሜጄር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑኩ በውይይቱ እየተካፈለ ይገኛል።

በውይይቱ በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ደህንነትን ለማጠናከር በቁልፍ የደህንነት ጉዳዮች እና ለቀጣይ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ማየትና በቀጣናው ባለው ወቅታዊና ወሳኝ የደህንነት ችግሮች ላይ መፍትሄና አቅጣጫ ለማስቀመጥ ፍኖተ ካርታ ይዘረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል በክልሉ የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታትና በአባል ሀገራት መካከል ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ትብብርን ለማጎልበት ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየት መቀጠሉን የሃገር መከላከያ ሠራዊት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመለክታል።


ردود الفعل
Top