በትግራይ ክልል ከ5 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቀሉ

2 Days Ago 190
በትግራይ ክልል ከ5 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቀሉ

በትግራይ ክልል 5 ሺህ 728 የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ከማህበረሰቡ ጋር የመቀላቀል ስራ መሰራቱን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ።

የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ከማህበረሰቡ ጋር የመቀላቀል ስራ ከተጀመረ አንድ ወር የሚጠጋ ጊዜ አስቆጥሯል።

በዚህም እስካሁን በተሰራው ስራ 6ሺህ 625 የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ማዕከል የገቡ ሲሆን 5 ሺህ 728ቱ ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቅለዋል።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የፕሮግራም ዕቅድና ክትትል ዳይሬክተር ኮሎኔል በላይ አበበ፤ የመቐለና የዕዳጋ ሀሙስ ማዕከላት የቀድሞ ተዋጊዎችን በመቀበል ስልጠና እየሰጡ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአደዋ አካባቢ የሚገኘው ሶስተኛውን ማዕከል ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ነው ብለዋል።

889 የቀድሞ ተዋጊዎች በማዕከላት ስልጠና እየወሰዱ ሲሆን እስከ መጪው የካቲት ወር መጨረሻ በመጀመሪያው ዙር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ማህበረሰቡ እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል።

በንብረቴ ተሆነ

 


Feedback
Top