በናምቢያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ተመረጡ

17 Days Ago 222
በናምቢያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ተመረጡ

በናምቢያ በተደረገ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኔቱምቦ ናንዲ ኒዳትዋህ በሃገሪቱ ታሪክ የመጀመሪዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ከገዢው ፓርቲ ስዋፖ እጩ ሆነው ቀርበው የነበሩት ኔቱምቦ በምርጫው ማሸነፋቸው በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት አድርጓቸዋል፡፡

ኔቱምቦ ላለፉት በርካታ ዓመታት በከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ሀገራቸውን ያገለገሉ ሲሆን አሁን ላይም የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደነበሩ ተጠቅሷል፡፡

የናምቢያ ምርጫ ኮሚሽን እንዳስታወቀው ኔቱምቦ በምርጫው ከተሰጠው ድምፅ ከ 57 በመቶ በላይ የሚሆነውን ድምፅ በማግነት ነው ማሸነፍ የቻሉት፡፡

በምርጫው ተፎካካሪያቸው የነበሩት ፓንዱልኒ ኢቱላ በበኩላቸው 26 በመቶ የመራጮችን ድምፅ ማግኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡


Feedback
Top