ከመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ልምዶችን በመቀመር ትርጉም ያለው ርምጃ መራመድ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

1 Mon Ago 196
ከመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ልምዶችን በመቀመር ትርጉም ያለው ርምጃ መራመድ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

ከተማዎቻችንን ለእድገት እና ለኑሮ ይበልጥ ምቹ ለማድረግ ከመጀመሪያው ምዕራፍ ልምዶችን በመቀመር ትርጉም ያለው ርምጃ ለመራመድ ተችሏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስምንት የኮሪደር አቅጣጫዎች እና 2879 ሄክታር በሚሸፍን ስፋት ላይ እየተሰራ ያለውን የሁለተኛውን ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራ ሪፖርት መገምገማቸውን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤አሁን በሦስት መሠረታዊ ኃላፊነቶች ላይ ማተኮር ይገባናል ብለዋል።

በዚህም በመጀመሪያ ለቀጣዩ ትውልድ ፍላጎት የተስማሙ ከተሞችን መገንባት፤ ሁለተኛ በመለወጥ ላይ ባሉት ከተሞች ከፍ ብሎ ማደግ የሚችል ትውልድ መቅረጽ፤ ሶስተኛም እነዚህን የዘመኑ ከተሞች በልህቀት ለመምራት የተዘጋጀ አመራር ኮትኩቶ ማብቃት ናቸው ሲሉ አብራርተዋል።


Feedback
Top