ኢትዮጵያ 4ኛው አለም አቀፍ ፋይናንስ ለልማት ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ቁርጠኛ ናት - አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ

9 Days Ago
ኢትዮጵያ 4ኛው አለም አቀፍ ፋይናንስ ለልማት ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ቁርጠኛ ናት - አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ

በኢትዮጵያ በመጪው ሃምሌ ወር የሚካሄደውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 4ኛው አለም አቀፍ ፋይናንስ ለልማት ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ ገለፁ።

አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና መሀመድ ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅት አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ፤ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 4ኛውን ፋይናንስ ለልማት ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በውይይታቸውም፤ በኢትዮጵያ እና በመንግስታቱ ድርጅት መካከል ስላለው ዘርፈ-ብዙ አጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይም መክረዋል፡፡

በተጨማሪም በዘላቂ የልማት ግቦች የትግበራ ሁኔታ፣ በመጪው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እና በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይም ውይይት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top