ለበዓል በየቤቱ የቁም እንስሳትን ማረድ ወይም በየአካባቢው ቅርጫ አድርጎ መከፋፈል ተከልክሏል በሚል የሚናፈሰው መረጃ ሐሰተኛ ነው

14 ቀን በፊት
ለበዓል በየቤቱ የቁም እንስሳትን ማረድ ወይም በየአካባቢው ቅርጫ አድርጎ መከፋፈል ተከልክሏል በሚል የሚናፈሰው መረጃ ሐሰተኛ ነው

በአዲስ አበባ ከትንሳዔ በዓል ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡ በየቤቱ የቁም እንስሳት እርድ በማካሄድ ወይም በየአካባቢው ቅርጫ በማድረግ የሚከፋፈልበት አሰራር ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑ ተገለጸ። 

ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም ዓይነት ክልከላ ያልተደረገ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። 

ይልቁንም በየአካባቢው በሕገወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ድርጊቱ በከተማው ነዋሪዎች ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብሏል ቢሮው። 

የከተማዋ ነዋሪዎች በዓላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳ አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሕገወጥ እርድ ላይ የሚሰማሩ አካላትን ለመከላከል በሚደረገው ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆኑ መልዕክት አስተላልፏል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top