የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

13 ቀን በፊት
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

ትንሳኤ በእርቅ የተሞላ የአዲስ ሕይወትና የአዲስ ምዕራፍ ማሳያ ነው መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገልጸዋል።

በዓሉ የሰላም፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ተመኝተዋል።

በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደማቁ የሚከበረው ትንሣኤ በበረከት የተሞላ የአዲስ ህይወትና አዲስ ምዕራፍ ተምሳሌት መሆኑ እንደሚታመን ገልጸዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ የተጓዘበት መንገድና ያሳያቸው የፍቅርና የሠላም ድርጊቶች ዝቅ ብሎ ማገልገልን፣ በትዕግስትና በመፈቃቀር ሁሉንም የሰው ልጅ ማክበርን እንደሆነ አውስተዋል፡፡

እነኚህን አስተምህሮዎችን በመከተል "እኛም በዓሉን ስናከብር የፍቅር፣ የመተሳሰብና የአገልጋይነትን ልቦና ተላብሰን ሊሆን ይገባል" ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ የብዝሃ ሃይማኖት ተከታይ ህዝቦች ባለቤት እንደመሆኗ ፥ የቆየውን የመቻቻል፣ የመከባበርና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆንም ተመኝተዋል ።

የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ፣ የክልሉ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የመደጋገፍ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዓሉን ስናከብር የተራበውን በማብላት፣ የታረዘውን በማልባስ፤ የታመመውን በመጠየቅ ፍቅርና አንድነትን በማሳየት ሊሆን ይገባልም ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top