ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ከገባች ጊዜ ጀምሮ የመጀመሪያው ይፋዊ ጉብኝት ያደርጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

2 Mons Ago 410
ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ከገባች ጊዜ ጀምሮ የመጀመሪያው ይፋዊ ጉብኝት ያደርጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሱዳን ሰላም ለማምጣት የሚደረገው ጥረት የሚያግዝ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በሱዳን የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን አድርገዋል።
 
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጉብኝት ለሱዳን መረጋጋት የሚያከናውኑት ጥረት ቀጣይ እርምጃ መሆኑን ጠቁሟል።
 
ይሄው በፖርት ሱዳን የተደረገው ጉብኝት ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ከገባች ጊዜ ጀምሮ በመሪ ደረጃ የተደረገ የመጀመሪያው ይፋዊ ጉብኝት ሆኗል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
 
የሱዳን ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አል ቡርሃን ጊዜያዊ ማእከላቸውን በፖርት ሱዳን ካደረጉ ወዲህ ለሀገር መሪ አቀባበል አድርገው በሀገራቸው የሰላም ጉዳይ ሲመክሩም የመጀመሪያ ነው።
 
"የወንድም ሱዳን ህዝብ ችግር የኛም ችግር ሰላማቸውም ሰላማችን በመሆኑ ለሱዳን ህዝብ እፎይታ እና የብልፅግና ጉዞ ዛሬም እንደ ትላንቱ ከልብ እንሰራለን።" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባለፈው ሳምንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የሱዳን ትክክለኛ ጎረቤት ሀገር መሆኗን ተናግረዋል።
 
ከሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች ጋር “ገለልተኛ አቋም በመያዝ ሁለቱም ሃይሎች ወደ ሰላም እንዲመጡ ስንሰራ ቆይተናል አሁንም በዚሁ መንገድ እንሰራለን” ማለታቸው የሚታወስ ነው።
 
የሱዳን ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አል ቡርሃን ጊዜያዊ መቀመጫቸውን ወደ ፖርት ሱዳን ማዛወራቸው ይታወቃል።

Feedback
Top