ሀገር በቀል ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎችን እና መለዋወጫዎችን ሲያመርቱ መመልከት በእጅጉ ያበረታታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመጠቀም፣ ጥራት ያላቸው ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ የኤሌትሪክ ገመዶችን እና የኤሌትሪክ ማማዎችን ለኤሌክትሪክ ብሎም ለቴሌኮም ዘርፎች በሀገር ውስጥ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑ ገልፀዋል።
የብረት ምርትን ማሳደግ የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ አካል መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የተሽከርካሪዎችን እና የመለዋወጫዎችን የምርት ሥራ በመመልከቴ ተደስቻለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሀገር በቀል ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎችን እና መለዋወጫዎችን ሲያመርቱ መመልከት በእጅጉ ያበረታታል ብለዋል።