ጥንታዊ ቅርሶችን ከዛሬ ጋር በማስተሳሰር ለነገ ለማሻገር ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

19 Hrs Ago 61
ጥንታዊ ቅርሶችን ከዛሬ ጋር በማስተሳሰር ለነገ ለማሻገር ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከያኒት ዓለም ፀሐይ ወዳጆ በመታደስ ላይ የሚገኘውን የቢትወደድ ኃ/ጊዮርጊስ ኃ/ሚካኤል የቀድሞ መኖሪያ ቤት፣ የመጀመሪያው የማዘጋጃ ቤት፣ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት፣ ከ119 ዓመታት በፊት የተገነባውን እና ለእቴጌ ጣይቱ የባህልና ትምህርት ማዕከል ሆኖ የሚያገለግ የቅርስ ቤት እድሳት ጎብኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን አስመልክቶ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፣ ከያኒት ዓለም ፀሐይ እያደረገች ላለችው ተምሳሌታዊ ሥራ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አብዛኛውን እድሳት በጥሩ ሁኔታ በመስራት ላይ እንደምትገኝ የገለጹት ከንቲባዋ ቀሪ ስራዎችን ደግፈን በተሻለ ሁኔታ ለቱሪስት መስህብነት እና ለታለመለት አላማ እንዲውል እናደርጋለን ብለዋል::

ትናንት ወረት መሆን የሚችሉትን ከዛሬ ጋር በማስማማት ለነገ እንዲተላለፍ በማለት  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤተ መንግስት እና በመላዉ ሀገሪቱ ያሉትን በማልማት እና በሀገሪቱ ያሉ ቅርሶች በተገቢው መንገድ በማደስ ማስጀመራቸውን ከንቲባዋ አውስተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ከተማ አስተዳደሩ እንደ አዲስ አበባ ጥንታዊ ቅርሶችን ከዛሬ ጋር በማስተሳሰር ለነገ ለማሻገር እድሳት የሚፈልጉት እድሳት በማድረግና በማዘመን ለቱሪዝም ስበት በሚያገለግል መልኩ በማስተዋወቅ፣ ሀብት ለማፍራት እንዲሁም ለትውልድ እንዲተላለፍ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ከአራት ኪሎ እስከ ፒያሳ የሚገኙ ቅርሶችን በአዲስ መንገድ በልዩ ሁኔታ በኮሪደር ልማት ስራ ማደሱን ገልፀዋል::

ማደስ፣ ማዘመን፣ ማስተዋወቅ፣ ቱሪዝምን በመጠቀም ሀብት መፍጠር እንዲሁም ትውልድ እንዲማርበት ማቆየት ተገቢ መሆኑንም ከንቲባዋ ጠቅሰዋል፡፡

ያረጀ እና አሮጌው ሁሉ ቅርስ ባለመሆኑ ፈርሶ ዘመኑን በሚዋጅ ደረጃ ማልማት አስፈላጊ ነዉ ሲሉም አክለዋል::

 

 


Feedback
Top