የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

14 Days Ago 208
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባኤው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ በመጀመሪያ ሶስት ወራት በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ በከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ማብራሪያ እንደሚቀርብ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ሹመቶች ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተመላክቷል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት በዚህ ጉባኤው የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ተጠቅሷል። 

የምክር ቤቱ አባል ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን የተነሣው በፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት መሆኑን በምክር ቤቱ የሰላም፣ የፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ አስታውቋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሚኒስቴሩ የቀረበውን የሙስና ክስ በመመርመር የደረሰበትን ውጤት ለምክር ቤቱ ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል።

ምክር ቤቱ የቀረበው ሪፖርትን በመመልከት አባሉ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

 


Feedback
Top