18 ሰዓት በፈጀ የቀዶ ህክምና በጭንቅላት ላይ የወጣ እጢን በተሳካ ሁኔታ ማስወገድ ተቻለ

8 Mons Ago 1497
18 ሰዓት በፈጀ የቀዶ ህክምና በጭንቅላት ላይ የወጣ እጢን በተሳካ ሁኔታ ማስወገድ ተቻለ

በአለርት ኮሞፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአንድ ወጣት በጭንቅላት ላይ የወጣ እጢን በተሳካ ሁኔታ ማስወገድ መቻሉ ተገለፀ፡፡

በተከናወነው የቀዶ ህክምና በወጣቱ ጭንቅላት ላይ የነበረውን 20 ሳንቲሜትር ከፍታ የለው እብጠት እንዲወጣ የተደረገ ሲሆን፤ እብጠቱ የወጣበትን ቦታ በሌላ የሰውነት ክፍል የመተካት ተግባር መከናወኑ ተጠቅሷል።

በቀደ ህክምናው ወቅት በሰውነት ክፍሉ የደም መፍሰስ ችግር እንዳይኖር አስቀድሞ በቂ ደም መያዝና የደም ስሮችን የመቋጠር ተግባር መከናወኑም ነው የተገለፀው፡፡

ታካሚው ከ18 ሰአታት በኋላ ወደፅኑ ህሙማን ክፍል እንዲቆይ የተደረገ ሲሆን፤ አሁን ላይ በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

በሆስፒታሉ የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ስፔሻሊስት ባለሙያና የማክሮ ሰርጀሪ ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር አብዱራዛቅ በዚህ ህክምና ላይ ለተሳተፉ አጠቃላይ ሰራተኞች ምስጋና  ማቅረባቸውን የአለርት ኮሞፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መረጃ አመልክቷል።


Feedback
Top