የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓለም ዙሪያ፣ ትውልዶችን የሚያስተሳስር ትሩፋት

4 Hrs Ago 57
የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓለም ዙሪያ፣ ትውልዶችን የሚያስተሳስር ትሩፋት

የኢትዮጵያ አርበኞች የድል ቀን በኢትዮጵያ የሚገኙ ብቻ ሳይሆኑ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የጣሊያንን ወረራ የተቃወሙትን ጀግኖች በማወደስ ያከብሩታል።

ከአዲስ አበባ እስከ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ከለንደን እስከ ሜልቦርን ድረስ የኢትዮጵያ አርበኞች መታሰቢያ በሰንደቅ ዓላማ ተሽቆጥቁጦ፣ በባህላዊ ዝግጅቶች እና በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች ይከበራል።

በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች በተለይም እንደ አሜሪካ እና እንግሊዝ ባሉ ሀገራት ቀኑን ለማክበር የባህል ዝግጅቶችን፣ ትምህርታዊ ፕሮግራሞችን እና የማኅበረሰብ ስብሰባዎችን ያዘጋጃሉ።

እነዚህ ዝግጅቶች በአብዛኛው የባህል ሙዚቃ፣ ውዝዋዜ እና በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያተኮሩ ንግግሮችን ያጠቃልላሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዓለም ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ወጣቶች  የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዓት በማዘጋጀት በአርበኞች መሥዋዕትነት የተቃኙ ግጥሞችን ያቀርባሉ።

በአካል ቢራራቁም በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ይህቺን የድል ቀን ያከብራሉ።

የኢትዮጵያ አርበኞች መታሰቢያን እያንዳንዱ ትውልድ - በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሆኖ  የተገኘውን ነፃነትን በአንድነት፣ በሙሉ ልብ እና በኩራት ያስታውሳል።

እንኳን ለ84ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ!

በሴራን ታደሰ


Feedback
Top