ነባሩ ፓስፖርት ምን ይሆናል?

20 Hrs Ago 140
ነባሩ ፓስፖርት ምን ይሆናል?

የኢሜግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት  አዲስ ኢ-ፓስፖርት ዛሬ ይፋ አድርጏል::

አዲሱ ኢ-ፓስፖርት የአንድን ግለሰብ ባዮሜትሪክ መረጃ ጨምሮ የጣት አሻራዎችን፣ የፊት ለይቶ ማወቂያ እና የኤሌክትሮኒክስ ቺፕስ ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ ታዲያ አሁን አገልግሎት ላይ ያለው ነባሩ ፓስፖርት ምን ሊሆን ነው? የሚል ጥያቄ ያስነሳል::

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ይፋ እንዳደረገው ነባሩ ፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜው እስከሚያበቃ ድረስ ስራ ላይ ይውላል::

ቀደም ሲል ፓስፖርት የነበራቸው የፓስፖርቱ የአገልግሎት ጊዜው እስኪያበቃ መጠቀም እንደሚችሉ ታውቋል::

አዲሱን ፓስፖርት መቀየር የሚፈልጉ ከሆነ ግን  አሻራ ከሰጡ በኋላ በአስር ቀናት ውስጥ ፓስፖርቱ በእጃቸው እንደሚገባ ነው የተገለፀው፡፡

በሂደት ግን ነባሩ ፓስፖርት በአዲሱ የኢ-ፓስፖርት እንደሚተካ አገልግሎቱ ይፋ አድርጏል::

ከዚህ ቀደም ለ125 አመታት ኢትዮጵያ ትጠቀምበት የነበረውን የማንዋል ፓስፖርት ወደቴክኖሎጂ ለመቀየር በማሰብ ነው አዲሱ ፓስፖርት ይፋ የተደረገው::

ንፍታሌም እንግዳወርቅ


Feedback
Top