Search

እንግዶች የአፍሪካን የጤና ራዕይ ወደፊት ለማራመድ ምድረ ቀደምት በሆነችው ኢትዮጵያ ተሰባስበዋል፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ሰኞ ኅዳር 14, 2019 22

የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ዋና ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ፣ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለውን 5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ (CPHIA 2026) በማስተናገድ ዳግም የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ማዕከል ሆናለች።

የጤና ጉባኤው “የአፍሪካ የጤና ደኅንነት እና ሉዓላዊነት፤ ከጤና ጥገኝነት እና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነት እና ጽናት የሚደረግ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በጉባኤው የሀገር እና የመንግሥት መሪዎች፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የአፍሪካን የወደፊት የጤና ራዕይ ወደፊት ለማራመድ ምድረ ቀደምት በሆነችው ኢትዮጵያ መሰባሰባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: