Search

የኢትዮጵያን የሰላም ማስከበር ሚና ለማስቀጠል የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር እየተደረገ ነው

ማክሰኞ ኅዳር 08, 2019 122

የኢትዮጵያን የሰላም ማስከበር ሚና ለማስቀጠል የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።

ምክክሩን በመከላከያ ሠራዊት የሰላም ማስከበር ማዕከል የዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢስቲትዩት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ  መከላከያ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁት።

ኢትዮጵያ 70 ዓመታትን በተሻገረው ታሪካዊ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ውስጥ 200 ሺህ የሚጠጉ ሠራዊቶቿን በማሰማራት ለዓለም አቀፍ ሰላም ትልቅ ሚና መጫወቷ በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

አሁን ላይ እየተቀየረ ባለው የዓለም አቀፍ ስርዓት ውስጥ የኢትዮጵያን የሰላም ማስከበር ሚና ማጠናከር እና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር መፍትሔ ለመፈለግ እንዲሁም ትብብርን በሚፈልጉ ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንዴት በጋራ መሥራት እንደሚቻል እየተመከረ ይገኛል።

በቶማስ ኃይሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: