Search

የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና በተግባር የሚቀንሱ የገበያ ማዕከላት

ማክሰኞ ኅዳር 08, 2019 135

በከተማችን አዲስ አበባ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ ማሟላት የሚያስችል ሁኔታ እየተመቻቸ ነው።

ይህንን መርህ በተግባር የሚያሳየው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በቀጥታ ለሸማቾች የሚቀርቡባቸውን  የገበያ ማዕከላትንና የቅዳሜና እሑድ ገበያዎች ተደራጅተዋል።

ከ282 በላይ የቅዳሜና እሑድ ገበያዎች መዘርጋታቸው የዚህ ጥረት አንዱ ጉልህ ውጤት ነው። በእነዚህ ማዕከላት ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ፍጆታቸዎች በሚያገኙበት አቅራቢያ፣ ያለአላስፈላጊ የጉዞ ወጪና የጊዜ ብክነት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት እየቻሉ ነው።

የአሠራሩ ዋነኛ ጥንካሬ ትኩስ ምርትን ከአምራቹ በቀጥታ ወደ ሸማቹ ማድረስ መቻሉ ሲሆን፣ በዚህም በምርት አቅርቦትና በሸማች መካከል የሚገቡ አላስፈላጊ የደላላ ሰንሰለቶችን በማሳጠር፣ የዋጋ መናርን ለመቀነስና ሸማቹ በተሻለ ዋጋ ምርት እንዲያገኝ ዕድል ተፈጥሯል።

ይህ አሠራር ሸማቹን ብቻ የሚጠቅም ሳይሆን አምራቹም ምርቱን በቀጥታ ለገበያ በማቅረብ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ያስችለዋል።

በዚህም የአምራችና የሸማች ትሥሥርን ከማጠናከር ባሻገር፣ የከተማና የገጠር ኢኮኖሚያዊ ትሥሥርንም አሳድጓል።

ከሁሉም በላይ እነዚህ የገበያ ማዕከላት የኑሮ ውድነትን በንግግር ብቻ ለመቋቋም ሳይሆን፣ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ፣ የገበያ ትሥሥሩን በማሻሻልና ሸማቹን በቀጥታ በመደገፍ በተግባር መፍትሄ የሚያመጡ ናቸው።

ለብዙ ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ወጪን ለማቃለል እውነተኛና ተደራሽ የገበያ አማራጭ መሆናቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: