Search

COP32 ብሔራዊ ጥረቶቻችንን ወደ ዘላቂ ውጤት ለመለወጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ ኅዳር 07, 2019 197

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት የCOP32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴን በመሰብሰብ አጠቃላይ የሥራ ሂደት መገምገማቸውን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በግምገማው ወቅት የCOP32 ዝግጅቶችን ከፈትሽን በኋላም ሥራዎች የሚመሩበት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ ሰጥቻለሁ ብለዋል።

ጉባኤውን በስኬት ለማስተናገድ ሁሉም ግብረ-ኃይሎች ተናብበው እንዲሠሩ በማድረግ፣ የተቀናጀ ሁሉን አቀፍ የመንግሥት አካሄድ መከተል ወሳኝ መሆኑን በአጽንዖት አሳስቤያለሁ ነው ያሉት።

COP32 ታላቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከመሆኑ ባለፈ፣ የኢትዮጵያን የአየር ንብረት እና የአካባቢ ጥበቃ አጀንዳን ለማራመድ፣ አጋርነትን ለማጠናከር፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እንዲሁም ብሔራዊ ጥረቶቻችንን ወደ ዘላቂ ውጤት ለመለወጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ሲሉም አብራርተዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: