ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ወደ ሰላማዊው መድረክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ

3 Days Ago 118
ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ወደ ሰላማዊው መድረክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ
ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ፅንፈኝነት እና ግጭት ማንንም እንደማይጠቅም በመገንዘብ ወደ ሰላማዊ መድረኩ እንዲመጡ ጥሪ እናቀርባለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
 
ዛሬ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች፣ የገጠር ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ህዝቡ "ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሀሳብ በነቂስ ወጥቶ ላሳየው የሰላም የድጋፍ ሰልፍ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።
 
ሰላም ወዳዱ ህዝባችን መንግሥት ለሰላም እያቀረበው ያለውን ተደጋጋሚ ጥሪ በመደገፍና ፅንፈኝነትን በማውገዝ የታጠቁ ቡድኖች ወደ ሰላም እንዲመጡ ጥሪ አቅርቧል ብለዋል አቶ ተመስገን።
 
በመሆኑም የአማራ ክልልን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁሉም ለሰላም ዘብ ሊቆም ይገባል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት።
 
መንግሥት ሁልጊዜም ቢሆን ለሰላም በሩ ክፍት በመሆኑ ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ፅንፈኝነት እና ግጭት ማንንም እንደማይጠቅም በመገንዘብ ወደ ሰላማዊ መድረኩ እንዲመጡ ጥሪ እናቀርባለንም ብለዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top