የኢትዮጵያ ምርቶች በጥሩ ዝግጅት የዓለምን ገበያ እንዲሻሙ መሠረት የጣልንበትን የ’ጥራት መንደርን’ ዕውን አድርገናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ዛሬ በንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የተገነባውን 'የጥራት መንደርን' መርቀን ከፍተናል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ገበያ በምታመርታቸው ምርቶች ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችላትን ሥራ ከመሥራት ተሻግራ የምርቶችን ደረጃ የምትቆጣጠርበት መንደር ገንብታለች ሲሉም ገልፀዋል።
የምርቶችን ጥራት ተፈትሾ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ምርቶች የሚወጡበት 'የጥራት መንደር' የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነት የሚያረጋግጡ ግዙፍ ሥራዎች በመሠራት ላይ መሆናቸውን ማሳያ መሆኑንም አመልክተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፤ የ’ጥራት መንደር’ ርዕዩን አመንጭተው ዕውን እንዲሆን ጠንካራ አመራር የሰጡትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) እና የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አመራሮችን አመስግነዋል፡፡