እንደ "ያሆዴ" ያሉ በዓላት ህዝቦችን የማስተሳሰር አቅም አላቸው - የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ

2 Mons Ago
እንደ "ያሆዴ" ያሉ በዓላት ህዝቦችን የማስተሳሰር አቅም አላቸው - የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ

እንደ "ያሆዴ" ያሉ በዓላት ህዝቦችን የማስተሳሰር አቅም አላቸው ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ።

ለሀዲያ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል እንኳን  በሠላም አደረሳችሁ  ብለዋል ሚኒስትሩ።

የሀዲያ ብሄረሰብ የረጅም ጊዜ ታሪክ እና ጠንካራ አደረጃጀት ያለው ህዝብ ነው ብለዋል።

ቀደምት አባቶቻችን ብዙ ዕውቀትና ታሪክ ትተውልን ሄደዋል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ዕውቀቶቹን ለሀገር ግንባታ እንዲሁም ለማህበረሰባዊ ትስስር ልንጠቀምባቸው ይገባል ብለዋል።

መሰረታዊ የሰው ልጅ ነፃነት ከምንላቸው ውስጥ ሰብዓዊ መብት፣ ማህበራዊ መብት እንዲሁም የባህልና የቋንቋ መብቶች ይጠቀሳሉ ያሉት ሚኒስትሩ፤ በዚህ ረገድ ያሆዴ ባህላዊ በዓል ነው ሲሉ አብራርተዋል።

በበዓሉ ውስጥ የሚካሄዱት ክዋኔዎች ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ በመሆኑ ለትውልድ ማስተማርና ማስተላለፍ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።