የቱሪዝም ሚኒስቴር በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች አምስት አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን እንደሚያስገነባ አስታወቀ

2 Mons Ago
የቱሪዝም ሚኒስቴር በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች አምስት አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን እንደሚያስገነባ አስታወቀ

የሚኒስቴሩ የህዝብ ግኑኙነት ዳይሬክተር ዶክተር ዓለማየሁ ጌታቸው እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም አቅም በሚፈለገው ደረጃ ጥቅም ላይ ማዋል ሳትችል ቆይታለች።

በመሆኑም አሁን ላይ መንግስት አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን በማስተዋወቅ ከዘርፋ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።

በዚህም የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ጎብኝዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን  ተናግረዋል።

የቱሪዝም ፍሰቱን ይበልጥ ለማሻሻልም ነባር የቱሪዝም ስፍራዎችን የማደስና አዳዲስ የማልማቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የገለጹት።

ከዚህ አኳያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተያዘው በጀት ዓመት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ህዝብን በማስተባበርና የፋይናንስ ምንጮችን በማፈላለግ አምስት አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን የማልማት ስራ እንደሚጀምር ጠቁመዋል። 

የሚለሙት የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች በቀጣይ ይፋ እንደሚደረጉም ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ "በገበታ ለሀገር" እና "በገበታ ለትውልድ" አማካኝነት እያከናወኑት ያለው የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን የማልማት ስራ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ በእጅጉ እንደሚሻሻልም ተናግረዋል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top