የ25 የገጠር ከተሞች የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻፀም 30.37 በመቶ ደርሷል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

2 Mons Ago
የ25 የገጠር ከተሞች የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻፀም 30.37 በመቶ ደርሷል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 25 የገጠር መንደሮችን/ከተሞችን በፀሃይ ኃይል ማመንጫ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚስችል የሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት ቀርፆ ወደ ስራ ገብቷል።

ፕሮጀክቱ ከሰባት ክልሎች በተመረጡ 25 የገጠር ቀበሌዎች የሚገነባ ሲሆን፤ ግንባታው በአራት ኮንትራክተሮች በ6 ሎት ተከፍሎ እየተከናወነ ይገኛል። 

የኦፍ ግሪድ ፕሮጀክቱ የገንዘብ ምንጭ የአፍሪካ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ መንግስት (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት) ሲሆኑ፤ አጠቃላይ ወጪው 20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እና 161 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ነው።

እየተገነባ ያለው ሶላር ፕሮጀክት ዋና ዓላማ ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ 25 የገጠር ቀበሌዎችን በፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ነው። 

ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲደረግ የዕውቀት ሽግግር እና ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን፤ 145 ሺህ 169 አዳዲስ ደንበኞችንም የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ያደርጋል። 

አጠቃላይ 8 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ይህ ፕሮጀክት፤ 68 ነጥብ 7 የመካከለኛና 233 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ይከናወንለታል።

ግንባታው በሁለት የቻይናና በአንድ የኮሪያ ኩባንያዎች እየተከናወነ ሲሆን፤ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻፀም አሁን ላይ 30.37 በመቶ መድሱን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top