ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ የባንክ እና የኢንቬስትመንት ዘርፎች አስፈላጊውን የአሰራር ማሻሻያ ለማድረግ በቁርጠኝነት ይሰራል - የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ

3 Mons Ago
ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ የባንክ እና የኢንቬስትመንት ዘርፎች አስፈላጊውን የአሰራር ማሻሻያ ለማድረግ በቁርጠኝነት ይሰራል - የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ

የኢትዮያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ከአውሮፓ ኅብረት ልዑክ መሪ አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ እና በኢትዮያ የአውሮፓ ኅብረት ንግድ ምክር ቤት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በኢትዮጵያ የገንዘብ ፖሊሲ፣ የባንክ ዘርፍ እና የኢንቬስተመንት ከባቢ ላይ ያተኮረ እንደነበር ከብሔራዊ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አቶ ማሞ ምህረቱ በውይይቱ ወቅት ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ ያለውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ የባንክ እና የኢንቬስትመንት ዘርፎች አስፈላጊውን የአሰራር ማሻሻያ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

ይህም በአገሪቱ በስራ ዕድል ፈጠራ እና በውጭ ምንዛሬ ግኝት ለተሰማሩ የአገር ውስጥ እና የውጭ ባለሀብቶች የተመቻቸ ሁኔታን እንደሚፈጥር አብራርተዋል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top