ኢትዮጵያ እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም የቆየ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

3 Mons Ago
ኢትዮጵያ እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም የቆየ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተጠባባቂ ተወካይ ክሪስ ኒኮይን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ተቋሙ በኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ላበረከተው ያላሰለሰ ሰብዓዊ ድጋፍ አምባሳደር ምስጋኑ አመስግነዋል።

የኢትዮያ መንግሥት በተለያዩ ምክንያቶች በችግር ላይ ለወደቁ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማዳረስ ያልተቆጠበ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ አጋር ሰብዓዊ ተቋማት በኢትዮጵያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ስደተኞች ዕርዳታ እንዲለግሱ ጠይቀዋል።

መንግሥት ከሁሉም ሰብዓዊ ተቋማት ጋር በቅርበት በመሥራት የዕርዳታ ስርጭቱን ፍትሐዊነት፣ ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት በሰፈነበት አግባብ ለማከናወን ቁርጠኛ እና ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተጠባባቂ ተወካይ ክሪስ ኒኮይ በበኩላቸው ተቋሙ ሰብዓዊ ድጋፉን በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በችግር ላይ ላሉ ዜጎች ለማዳረስ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ሁለቱ ወገኖች በጋራ በአገሪቱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን መድረስ ይችሉ ዘንድ የቆየ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top