አሜሪካ በትምህርት ተቋማቷ ውስጥ እየተስፋፋ የመጣውን የጅምላ ተኩስ ግድያ ማስቆም ለምን ተሳናት?

1 Yr Ago 2286
አሜሪካ በትምህርት ተቋማቷ ውስጥ እየተስፋፋ የመጣውን የጅምላ ተኩስ ግድያ ማስቆም ለምን ተሳናት?

ሰኞ ዕለት በሰሜን ካሮላይና በሚገኘው አንጋፋው ቻፕል ሂል ዩኒቨርሲቲ  በአንድ  ግለሰብ ጅምላ ተኩስ ተከፍቶ አካባቢውን የጦር ቀጣና አስመስሎት ነበር፡፡

ፈርስት ፖስት እንደዘገበው፥ ተኩሱ የተከፈተው በግቢው መሀል ከሚገኙት የሳይንስ ሕንፃዎች በአንዱ ውስጥ ሲሆን፣ የተኩሱ መንስዔ እስካሁን አልታወቀም።

ዘገባው ተማሪዎች እና መምህራን በዶርም፣ በመታጠቢያ ቤት፣ በመማሪያ ክፍል እና በጂም ውስጥ ተደብቀው ሲያለቅሱ ያሳያል።

ተኳሹ በፖሊስ ከመያዙ በፊት አንድ ፕሮፌሰር የገደለ ሲሆን፤ በተኩሱ ወቅት ተማሪዎች ከኮሌጁ ለማምለጥ በመስኮት ሲዘልሉ እንደታዩ ዘገባው ያመለክታል።

ሌሎች ተማሪዎች እና አስተማሪዎች ንቁ ተኳሽ መሆን ከዚህ አደጋ እንደሚያድናቸው በማመን ልምምድ ላይ መሆናቸውን እና ይህ ሁኔታም በአሜሪካ እንደ መፍትሔ እየተወሰደ እንደሆነ ዘገባው ይጠቁማል።

የዩኒቨርሲቲው ቻንስለር ኬቪን ጋስኪዌስ እንደገለጹት፥ ተኩሱ የተከፈተው በአንድ ላቦራቶሪ ውስጥ ሲሆን፣ ተጠሪጣሪው በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡

ቻንስለሩ አንዱ የፋኩሊቲያቸው አባል በተኩሱ መገደሉን ገልጸው፣ በደረሰው ሁኔታ ከልብ ማዘናቸውን ተናግረዋል።

አክለውም፥ ክስተቱ በጣም መጥፎ እና የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብ ደህንነት ስጋት ውስጥ የጣለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አንዷ፥ “በመጀመሪያ ነገሩ እንደዚህ ከባድ አልመሰለንም ነበር፤ በግቢው ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ እየተለወጠ ሲመጣ፣ ራሳችንን ለማዳን መሮጥ ጀመርን” ብላለች፡፡

ሌላኛው ተማሪ ደግሞ ሁኔታውን ሲገልጽ፥ “ላቦራቶሪ ውስጥ ነበርን፤ በግቢው ውስጥ ተኩስ መከፈቱን በክፍሉ ውስጥ ከነበረው ፕሮጄክተር ላይ አየን፤ ከዚያም የክፍሉን በር ዘጋን” ብሏል፡፡

በአሜሪካ በትምህርት ተቋማት ውስጥ ጅምላ ተኩስ አዲስ አለመሆኑን ያስታወሰው ዘገባው፣ እ.ኤ.አ በ2007 በቨርጂኒያ 33 ሰዎች የሞቱበትን፣ እ.ኤ.አ በ2012 በኮኔክቲከት ሳንዲ ሁክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 28 ሰዎች የተገደሉበትን፣ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በቴክሳስ ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 22 ሰዎች የሞቱበትን፣ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ በሚችጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ 4 ሰዎች የሞቱበትን የጅምላ ተኩስ ግድያዎች ጠቅሷል፡፡

እንደ ዘገባው፥ ቁጥሩ እየጨመረ የመጣው የጅምላ ተኩስ በአሜሪካ ከፍተኛው የሞት ምክንያት እየሆነ መጥቷል፡፡

“ነገር ግን” ይላል ዘገባው፥ “ነገር ግን አሜሪካ ለችግሩ ዘላቂ መፍተሔ ከመፈለግ ይልቅ ተማሪዎች እንዴት ወንበር ስር ተደብቀው ከግድያ ማምለጥ እንደሚችሉ በማስተማር፣ ለሟቾች ሻማ በማብራት እና በፀሎት በማሰብ ውስጥ ተደብቃለች፤ ታዲያ፥ ተማሪዎቹ እንዴት ከጅምላ ተኩስ ራሳቸውን ማዳን እንዳለባቸው ረስተው ቢሸበሩ ሊወቀሱ ነውን? መፍትሔውስ የአሜሪካ አይነኬ የጦር መሳሪያ ባህልን ለመቀየር መሥራት፤ ወይስ የሥልጣን ጥጋቸውን ይዘው በዝምታ የሚመለከቱ ባለሥልጣናቷን ማንቃት?” በማለት ይጠይቃል - ዘገባው፡፡


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top