የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከፍተኛ መኮንኖች አዲሱን የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ጎበኙ

4 Mons Ago
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከፍተኛ መኮንኖች አዲሱን የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ጎበኙ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 4ኛ አየር ምድብ ከባህርዳር የመጡ ከፍተኛ መኮንኖች አዲሱን የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ጎበኙ።

የአየር ኃይል 4ኛ ምድብ አባል የሆኑት ኮሎኔል ሃብቴ አባድልቢ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት ተቋሙ እየሄደበት ያለው የለውጥ ጉዞ አስደናቂ ነው ብለዋል።

አየር ኃይል እና ኢቢሲ 24 ሰዓት በሀገር ጉዳይ በንቃት የሚሰሩ መሆናቸው እንደሚያመሳስላቸውም ገልጸዋል።

ከደብረዘይት አየር ኃይል የመጡት የተዋጊ እና የትራንስፖርት ሄሌኮፕተር አብራሪ ሻለቃ ገመቹ ሀሰን በበኩላቸው በተቋሙ ለውጥ እጅግ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ተቋሙ እንደ አየር ኃይልም አንጋፋ ከመሆኑ አንፃር የምንኮራበት ነው ያሉት ሻለቃ ገመቹ በቀጣይ የሀገር ግምባታ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል።

በላሉ ኢታላ


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top