ደቡብ አፍሪካ "የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በቁጥጥር ሥር ማዋል ጦርነትን ማወጅ ነው" አለች

1 Yr Ago 707
ደቡብ አፍሪካ "የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በቁጥጥር ሥር ማዋል ጦርነትን ማወጅ ነው" አለች

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎዛ የብሪክስ ሀገራት ስብሰባን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚካሄደውን ጉባኤ የሚታደሙትን የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በሀገሪቱ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ማሰብ ጦርነትን ማወጅ መሆኑን ተናግረዋል።

በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የሚፈለጉት ፕሬዚዳንት ፑቲን ሞስኮን ለቀው ከወጡ በፍርድ ቤቱ አባል ሀገራት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የሚያስገድድ ሕግ አለ።

ደቡብ አፍሪካ የብሪክስ ሀገራት ጉባኤን ለማስተናገድ አንድ ሳምንት የቀራት ሲሆን፤ ፑቲን በጆሃንስበርግ በሚካሄደው ጉባኤ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

ታዲያ ደቡብ አፍሪካም ፕሬዚዳንት ፑቲንን አሳልፋ ትሰጣለች? የሚለው ጥያቄ በተደጋጋሚ ሲነሣ ሰንብቷል ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top