ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የመሰረተ ልማት ንቅናቄን አስጀመሩ

1 Yr Ago 467
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የመሰረተ ልማት ንቅናቄን አስጀመሩ

“ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ቃል በከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብረሀም በላይ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እንዲሁም የከተማው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሻሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሂዷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ትምህርት ላይ የሚሰሩ ስራዎች ሀገር የሚገነቡ ተግባራት እንደመሆናቸው በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዛሬው ማስጀመሪያ መርሀ ግብር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል አደራ የተቀበሉ ክፍለ ከተሞችም ሆኑ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ማሻሻል ትውልድን የመስራት ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም አካል ያላሰለሰ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሻሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የህንጻ ግንባታ መሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን የከተማው ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመለክታል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top