ለመጀመሪያ ጊዜ በአገውኛ ቋንቋ የተሠራው "አንታጉ" ፊልም ተመረቀ

5 Mons Ago
ለመጀመሪያ ጊዜ በአገውኛ ቋንቋ የተሠራው "አንታጉ" ፊልም ተመረቀ

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ለመጀመሪያ ጊዜ በአገውኛ ቋንቋ የተሠራው "አንታጉ" የተሰኘው አገውኛ ፊልም የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና ታዋቂ አርቲስቶች በተገኙበት ተመርቋል።

የአዊ ብሔረሰብ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንግዳ ዳኛው በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የአገው ሕዝብ የታሪክ፣ የሥልጣኔ እና የቱባ ባህል ባለቤት ነው ብለዋል።

"አንታጉ" የአገውኛ ፊልምን ሠርተው የብሔረሰብ አስተዳደሩን ባህል፣ ታሪክ እና ቋንቋ ለዓለም ለማስተዋወቅ ለተሳተፉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

የፊልሙ ደራሲ አቶ ደሳለኝ መኩሪያው፣ "አንታጉ" ፊልምን ለመሥራት ከአንድ ዓመት በላይ ጊዜ የወሰደ መሆኑን ጠቅሰው፣ በአገውኛ ቋንቋ የተለያዩ ጹሑፎች እና ዘፈኖች ቢዘፈኑም በቋንቋው ፊልም ያልተሠራ በመሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊልም ሠርተው ለእይታ ማብቃታቸውን ተናግረዋል።

የተሠራው ፊልም የገጠሩን ገፀ-ባህርይ የያዘ መሆኑን የገለጹት ደራሲው፣ “በቀጣይ ማኅበረሰቡ የሚደግፈን ከሆነ በርካታ ፊልሞችን ለመሥራት ፈቃደኛ ነን” ማለታቸውን ከአዊ ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

"አንታጉ" የአገውኛ ፊልም ወጣት ደሳለኝ መኩሪያው በዳይሬክተርነት እና በተዋናይነት፣ የአዊ አምባሳደር መልካም ዘመን እና የዞኑ ባህል እና ቱሪዝም ሠራተኞች የተሳተፉበት ነው።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top