ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ14ኛው የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገቡ

5 Mons Ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ14ኛው የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ14ኛው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና መንግሥታት መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጁቡቲ ሲደርሱ የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በጉባኤው የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች እና ባለስልጣናት የሚሳተፉ ሲሆን ቀጣናዊ ተቋሙ በምስራቅ አፍሪካ እየተከናወኑ ላሉ ስራዎች እየሰጠ ያለውን ምላሽ ጨምሮ በተለያዩ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል።

በሮዛ መኮንን


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top